ወንጌል መስበክ ያለበት ማን ነው?

አንዳንድ ሰዎች የወንጌል ስብከት ተግባርን ለሰባኪዎች፣ ለአቅበተ-እምነት አስተማሪዎች፣ ወይም ለመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ብቻ ትተውታል። ነገር ግን አዲሱ ኪዳን ሁሉም ክርስቲያን አገልጋይ እንደሆነ እና ወንጌልን ሊሰብክ እንደሚገባ ይናገራል።

• ምሳሌ ትተውልናል፦ የመጀመሪያዋቹ ክርስቲያኖች በኑሯቸው ሁሉ ወንጌልን ይሰብኩ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፦ “የተበተኑትም በሄዱበት ሁሉ ወንጌሉን ተናገሩ” (ሐዋሪያት ሥራ 8፥4፤ ሐዋሪያት ሥራ 11፥19-21)። ሁሉም ደቀ መዛሙርት ከኢየሩሳሌም በተበታተኑ ጊዜም ወንጌሉን እየተናገሩ እንደነበር እናነብባለን።

• ታዝዘናል፦ ጴጥሮስ በመልእክቱ፣ “በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን በፍርሀት እና በየዋህነት ይሁን” ይለናል(1ኛ ጴጥሮስ 3፥15)።

• ፍቅር ግድ ይለናል፦ ጎረቤታችንን እንደ ራሳችን መውደድ ካለብን (ማርቆስ 12፥31፤ ያዕቆብ 2፥8)፣ ወንጌልን ለእርሱ/ሷ ከመናገር በላይ እውነተኛ መውደድ ከየት ይገኛል?