የ”ገላጭ” ስብከት መጽሐፍ ቅዱሳዊነት
ገላጭ ስብከት ምንድን ነው? አንድ ስብከት ገላጭ ስብከት ነው የምንለው የስብከቱ ይዘትና ዓላማ በምናካፍለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይዘትና ዓላማ ቁጥጥር ሥር ሲሆን ነው። ሰባኪው ማለት የሚችለው ክፍሉ የሚለውን ብቻ ነው፤…
ገላጭ ስብከት ምንድን ነው? አንድ ስብከት ገላጭ ስብከት ነው የምንለው የስብከቱ ይዘትና ዓላማ በምናካፍለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይዘትና ዓላማ ቁጥጥር ሥር ሲሆን ነው። ሰባኪው ማለት የሚችለው ክፍሉ የሚለውን ብቻ ነው፤…
ሰባኪዎች ለማን ነው የሚሰብኩት? በቅርብ ብዙ ስለ ስብከት የተጻፉ መጻሕፍትን ከመደርደሪያዬ ላይ አውርጄ እያገላበጥኩ ነበር፤ እናም የተገለጠለኝ ነገር ቀድሜ የጠየቅኩትን ጥያቄ ብዙም ሲመለከቱት አላየሁም። ሰባኪዎች አብዛኛውን ጊዜ ትኩረት የሚሰጡት ስብከታቸውን…
መልስ ገላጭ ስብከት የምንሰብከውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማዕከላዊ ሐሳብ የስብከቱ አንኳር ሐሳብ በማድረግ፣ አሁን ላለ ነባራዊ ሁኔታ የሕይወት ተዛምዶ የሚሠራበት የስብከት ዐይነት ነው። በሌላ አነጋገር፣ ገላጭ ስብከት የአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ…
ፊሊፕ ብሩክስ በታዋቂው የስብከት ትርጉሙ፣ “ስብከት ማለት እውነትን በማንነታችን ማስተላለፍ” ነው ሲል ተናግሯል፤ እንዲህ ብሎ ሲናገር ስለ አንድ ሰው የራሱ ማንነት እንጂ ስለ ሌላ ሰው ማንነት እያወራ እንዳልሆነ አምናለሁ። ብዙ…
ይህ ጥያቄ በማገለግልበት ቤተ ክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን መሪዎች እና ከተማሪ ሕብረት መሪዎች ብዙ ጊዜ የምሰማው ጥያቄ ነው። እና ለእነርሱ (ለአንባቢም) ከጽሑፉ በቀጥታ ወደ ነጥቡ፣ ወይም በተሻለ ሁኔታ ወደ ተግባራዊ ተዛምዶው የሚወስዳቸውን አስማታዊ ቀመር እንዳለኝ ከመናገር የበለጠ ደስታ የለኝም።
ባለፉት ዓመታት በዓለም ውስጥ ባሉ ትልልቅ አብያተ ክርስቲያናት የሚሰበከው መልእክት ተቀይሯል። በርግጥም በአሁኑ ጊዜ ብዙ ጉባኤዎች አዲስን ወንጌል እየተማሩ ነው። ይህ ወንጌል ብዙ ስሞች ይሰጠዋል፤ ለምሳሌ “ጥራው! የእኔ ነው በለው!” ወንጌል፣ “ንጠቅና ያዘው” ወንጌል፣ “የጤናና ሀብት” ወንጌል፣ “የብልጽግና ወንጌል” እና “የአዎንታዊ አዋጅ አስተምህሮ” ናቸው።
“ወደ ገነት እየጠቆምክ አትስበካቸው፤ አልያም ወደ ሲኦል። ነገር ግን ለታዳሚዎቹ ወንጌሉን ብቻ ስበክ።” ይህ በማላውቀው ሰው የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ስለመስበክ ያገኘሁት ጠቃሚ ምክር ነው። የቀብር ሥነ ሥርዐታችን ምንም ዐይነት ቢሆን፣ ይህ ለተግባራችን ወሳኝ መርህ ነው። በቀብር ሥነ ሥርዐቶቻችን ላይ ትኩረታችን የሟቹን ሕይወት ማክበርና ማስታወስ ቢሆንም፣ በዋነኛነት ግን ሥነ ሥርዐቱ ለታደሙት ሊሆን ይገባል።
አብዛኛውን ጊዜ ስብከቶች የሚያተኩሩት፣ የተሳካ ትዳር ለመመሥረት ወይም በባሕላችን ልጆችን ማሳደግ የሚቻልበት መንገድ ላይ ነው። በርግጥ በቤተሰብ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ስብከቶች ተስማሚ እና አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ሁለት ችግሮች ይከሰታሉ። በመጀመሪያ፣ ቅዱሳን ጽሑፎች ስለ እነዚህ ጉዳዮች የሚናገሩት ነገር በአብዛኛው ችላ ይባላል። ምን ያህሎቹ ስብከቶች ጳውሎስ ስለ ወንዶች እና ሴቶች ሚና ምን እንደሚል በታማኝነት እና በአስፈላጊ ጊዜ ይናገራሉ (ኤፌሶን 5፥22-33)? ወይስ ቅዱሳት መጻሕፍት በሚናገሩት እናፍራለን? ሁለተኛ፣ እና ምናልባትም ከዚ በከፋ ሁኔታ፣ እንደዚህ ዐይነት ስብከቶች የሚሰበኩት (ሁልጊዜም ማለት ይቻላል) በአግድመት ደረጃ (horizontal level) ነው።