ብቸኛው የመዳን መንገድ በክርስቶስ ማመን ነውን?

መልስ

ከባህል በኩል ያለ ተግዳሮት፦ በአሁኑ ዘመን ያሉ ሰዎች ሁሉን አካታች መሆን ይወዳሉ። ሁሉም ሰው ትክክል እንዲሆን እንፈልጋለን። ጭራሽ ብቸኛው ሰው ሊሳሳትበት የሚችልበት መንገድ፣ ሌላ ሰው ስለ ማንኛውም ነገር ተሳስቶ ሊሆን ይችላል ብሎ ካሰበ ነው ብለን እናስባለን። ስለዚህም ስለ ሃይማኖት ሲነሣ፣ “ሁሉም መንገዶች ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ። አንድ ብቻ ትክክለኛ መንገድ የለም። የሚያስኬድህ ነገር ሁሉ ለማመን ትክክለኛው ነገር ነው” ይባላል። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ይላል?

አጭሩ መልስ፦ ሐዋርያት ሥራ 4፥12 ላይ ጴጥሮስ፣ “ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።”

ትንሽ ረዘም ያለ መልስ፦ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ጻድቅ ልንቆጠር የምንችለው በክርስቶስ በማመን ብቻ ስለሆነ፣ በክርስቶስ ማመን ብቸኛው የመዳን መንገድ ነው (ገላቲያ 2፥16)። በክርስቶስ በማመን ብቻ ነው ከእግዚአብሔር ጋር ልንታረቅ የምንችለው (ሮሜ 5፥9–11)። በክርስቶስ በማመን ብቻ ነው የዘላለም ሕይወትን መቀበል የምንችለው (ዮሐንስ ወንጌል 3፥16)። ኢየሱስ ብቻ ነው በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል አስታራቂ (1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5)።

እውነተኛ አካታች፦ ምንም እንኳ ብዙ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ይሄንን መልእክት ለመቋቋም በሚከብድ መልኩ አግላይ ሆኖ ቢያገኙትም፣ መሠረታዊ ወደ ሆነው የወንጌል አካታችነት ልንጠቁማቸው ይገባል። ወንጌል ሁሉም ሰው ኀጢአተኛ መሆኑን በመናገር፣ ከኀጢአታቸው ዘወር ብለው በክርስቶስ ለሚታመኑ ይቅርታን እና የዘላለም ሕይወትን ይሰጣል። ከዚያ በፊት ምንም ያህል ጥሩ ወይም መጥፎ ብትሆን ለውጥ የለውም። ከየትኛውም አካባቢ መምጣትህ ወይም በፊት ትከተለው የነበረው ሃይማኖትም ለውጥ አያመጣም። ኀጢአትህን ብትናዘዝ እና በክርስቶስ ብታምን ትድናለህ።