ለቸልተኞች፣ ለተጠራጣሪዎች እና ለኃጢአተኞች መስበክ

ብዙ ጊዜ “ቅዱሳን መጻሕፍት በገላጭ ስብከት እንዴት ይተገበራሉ?” የሚል ጥያቄ እሰማለሁ። ከዚህ ጥያቄ ጀርባ ብዙ መነሻ ሐሳቦች ሊኖሩ ይችላሉ። ጠያቂው ይህን የሚለው፣ የሰማውን (ወይም የሰበከውን) “ገላጭ” ስብከት ነገር ግን በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ውስጥ በሚገባ ከተዋቀረ ሌክቸር ምንም ልዩነት የሌለው ንግግር፣ መጋቢያዊ ጥበብ እና የመልእክቱ አንገብጋቢነት የማያሳይን ስብከት እያስታወሰ ሊሆን ይችላል። እነዚህ የሰማቸው ገላጭ ስብከቶች ጥቂት ተግባራዊ ሐሳብ ስለኖራቸው ወይም ጠያቂው የስብከቱን ተግባራዊ ሐሳብ እንዴት መለየት እንዳለበት ላያውቅ ይችላል።

በካምብሪጅ የኖረው ታላቁ የዐሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን የፒዩሪታን የሥነ መለኮት ምሑር ዊልያም ፐርኪንስ ሰባኪዎች ለስብከታቸው የተለያዩ ዐይነት ሰሚዎችን እንዲገምቱ እና ለእያንዳንዱም እንደየ ፈርጁ- ልበ ደንዳና ኃጢአተኞች ፣ ተጠራጣሪዎች ጠያቂዎች ፣ የደከሙ ቅዱሳን ፣ ወጣት ተስፈኞች ፣ ወዘተ… እንዲያስቡ እና ተግባራዊ ሐሳብን እንዲያዘጋጁ ይመክራል።

የፐርኪንስ ምክር በጣም ጠቃሚ ነው፤ እንደዚህም እያደረግን እንዳለ ተስፋ አደርጋለሁ። የመተግበሪያውን ርዕሰ ጉዳይ በመጠኑም ቢሆን በተለየ መንገድ መቅረብ እፈልጋለሁ። እርሱም የተለያዩ ዐይነት ሰሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ ዐይነት መተግበርያዎች አሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ምንባብ ወስደን በግልጽ፣ በአሳማኝ፣ በአንገብጋቢ ሁኔታ ስናብራራ በክርስቲያናዊ ጉዞ ውስጥ የሚያጋጥሙ ሦስት የተለያዩ ችግሮችን የሚያንፀባርቁ ቢያንስ ሦስት የተለያዩ መተግበርያዎች አሉ። አንደኛ፣ የምንታገለው ቸልተኝነትን ነው። ሁለተኛ፣ መጀመሪያ ከገመትነው በላይ ብዙ ጊዜ ከጥርጣሬ ጋር እንታገላለን። ሦስተኛ፣ በቀጥታ ከኃጢአት ጋር እንታገላለን። ይህም እያወቁ ካለመታዘዝ ጋር ወይም ስለ ኃጢአት ያለ ቸልተኝነት ጋር ሊሆን ይችላል። ሰባኪ እንደመሆናችን መጠን የአምላክን ቃል በምንሰብክበት ጊዜ ሁሉ በራሳችንም ሆነ በአድማጮቻችን ላይ በሦስቱም አይነቶች ለውጦችን ለማየት እንፈልጋለን። ሦስቱም ችግሮች የተለያዩ ትክክለኛ መተግበርያዎችን ይፈልጋሉ።

ቸልተኝነት

በወደቀው ዓለም ውስጥ ቸልተኝነት መሠረታዊ ችግር ነው። እግዚአብሔርን ከእኛ ዓለም አርቀነዋል። ከፈጣሪያችን ጋር ህብረት ከማድረግ ራሳችንን አቋርጠናል። እንግዲያው ለሰዎች ስለ እግዚአብሔር እውነቱን ማሳወቅ በራሱ ሁነኛ የአተገባበር ዓይነት ሲሆን እኛ በጣም የሚያስፈልገን ይህ መሆኑ ምንም አያስደንቅም።

ይህ ለቀዝቃዛ ወይም ስሜት አልባ ስብከት ማስተባበያ ለመስጠት አይደለም። ለምክራዊ ስብከቶች እንደሆነው ሁሉ ለማስጠንቀቂያ መልእክቶችም በሙሉ እውነተኛ ስሜት ማገልገል እችላለሁ። የወንጌል ትዕዛዛት ማለትም ንስሓ መግባት እና ማመን ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ እኛ እና ስለ ክርስቶስ ከተናገሩት አስተንትኖት መግለጫዎች ውጪ ልንረዳቸው አንችልም። መረጃ ወሳኝ ነው። የተጠራነው እውነትን እንድናስተምር እና ስለ እግዚአብሔር ታላቅ መልእክት እንድናውጅ ነው። መልእክቶቻችንን የሚሰሙ ሰዎች ከአለማወቅ ወደ እውነተኛ ዕውቀት እንዲሸጋገሩ እንፈልጋለን። እንዲህ ዓይነቱ ከልብ የሆነ የማስተማር ይዘት በራሱ አንዱ መተግበርያ ነው።

ጥርጣሬ 

ጥርጣሬ ከቸልተኝነት የተለየ ነው። በጥርጣሬ ጊዜ የምናውቃቸውን ሐሳቦች ወይም እውነቶች መልሰን እንጠይቃለን።
ይህ ዓይነቱ ጥያቄ በክርስቲያኖች ዘንድ ብርቅ አይደለም። በእርግጥ፣ በስብከታችን ውስጥ በአስተሳሰብ ሊመረመሩ እና ሊሞገቱ ከሚገባቸው ጉዳዮች አንዱ ጥርጣሬ ሊሆን ይገባል። ጥርጣሬን መፍታት ሰባኪ ከማያምኑት ጋር ብቻ የሚያደርገውን የእቀበተ እምነት ስራ አይደለም። በየሳምንቱ ስብከቶችን ለማዳመጥ የሚቀመጡ አንዳንድ ሰዎች ሰባኪው ስለ ክርስቶስ ወይም እግዚአብሄር ወይም አናሲሞስ የጠቀሰውን ሁሉንም እውነታ በሚገባ ያውቁ ይሆናል፤ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች እውነት ይሁኑ አይሁኑ እያሉ ለማመን ይቸገራሉ። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ጥርጣሬያቸውን ሊገልጹት ይቅርና ጥርጣሬ እንዳላቸው ላይታወቃቸው ይችላል።

ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍትን በጥልቀት መመርመር ስንጀምር፣ ጥያቄዎች፣ እርግጠኛ ያልሆኑ ነገሮች እና ማመንታት፣ እናገኛለን። እነዚህ ሁሉ የጥርጣሬ ግፊቶች ከታማኝነት ጉዞ ሊያርቁን እንደሚችሉ እንድናውቅ ያደርጉናል። ለእንደዚህ ዐይነት ሰዎች- ምናልባት ለእንደዚህ ዐይነት የልባችን ውቅር፣ የእግዚአብሔርን ቃል እውነትነት እና የማመንን አንገብጋቢነት ልንከራከር እና ልናሳስብ እንወዳለን። የተጠራነው የእግዚአብሔርን ቃል እውነትነት ለሰሚዎች ልናበስር ነው። መልእክቶቻችንን የሚሰሙ ሰዎች ከጥርጣሬ ወጥተው በሙሉ ልብ በእውነት እንዲያምኑ እንፈልጋለን። እንዲህ ዓይነቱ ሞጋች ፣ ስለ እውነት እንድናስብ የሚያደርጉ ስብከቶች ሌላ ዐይነት መተግበርያ ናቸው።

ኃጢአት

ኃጢአት በዚህ በወደቀው ዓለም ውስጥ ሌላኛው ችግር ነው። ቸልተኝነት እና ጥርጣሬ በራሳቸው ኃጢአቶች ወይንም የህጥያት ፊሬዎች ሊሆኑ ውይንም ደግሞ ሁለቱንም አማራጭ ላይሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ኃጢአት በእርግጠኝነት ከቸልተኝነት ወይም ከጥርጣሬ በላይ ነው።

ስብከትህን የሚሰሙ ሰዎች ባሳለፉት ሳምንት ውስጥ እግዚአብሄርን ከመታዘዝ ጋር እንደሚታገሉ እና ቀጣይ ሳምንትም እርሱን ከመታዘዝ ጋር እንደሚታገሉ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። ኃጢአቶቹ የተለያዩ ናቸው። አንዳንዶቹ ተግባራዊ አለመታዘዝ ይሆናሉ፣ ሌሎች ደግሞ ያለመተግበር አለመታዘዝ ይሆናሉ። ነገር ግን የማድረግም ሆነ ያለማድረግ ፤ ኃጢአት ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ነው።
የእግዚአብሔርን ሕዝብ በቅድስና እንዲኖር እና የእግዚአብሔርን ቅድስና የሚያንፀባርቅ ሕይወት እንዲኖር መጠየቅ የስብከት አካል ነው። ሰሚዎቻችን ከሀጥያተኛ አለመታዘዝ ወደ የደስታ መታዘዝ እንዲመጡ እና በቃሉ እንደተገለጸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲታዘዙ እንፈልጋለን። እንዲህ አይነቱ ለጽድቅ ያለ ምክር በረግጥም መተግበርያ ነው።

ወንጌል

በምንሰብክበት ጊዜ ሁሉ መተግበር ያለብን ዋናው መልእክት ወንጌል ነው። አንዳንድ ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ምሥራች ገና አያውቁም። አንዳንዶቹ ደግሞ ስብከታችሁን እየሰሙ ሀሳባቸው ተበታትኖ፣ በቀን ቅዠት ውስጥ ሆነው ወይንም ሀሳባቸው በሌላ ነገር ተወስዶ ይሆናል። ስለዚህ ስለ ወንጌል ሁሌም ልንናገር ይገባል።
ሌሎች ደግሞ ሰምተው፣ ተረድተውት እና ምናልባትም እውነቱን ተቀብለው ሊሆን ይችላል፣ አሁን ግን በመልእክትህ ውስጥ የምትናገረውን ጉዳዮች በመጠራጠር እየታገሉ ይሆናል። እንደነዚህ ያሉት ሰዎች የክርስቶስን ምሥራች እውነት በማመን እንዲጸኑ ማስታውቅ ያስፈልጋል። 

አንዳንድ ሰዎች ወንጌል ሰምተው እና ተረድተው ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ለኃጢአታቸው ንስሃ ለመግባት የዘገዩ ይሆናሉ። ምናልባት የወንጌልን መልእክት እውነት ሊቀበሉ ቢወዱም ኃጢአታቸውን ለመተው እና በክርስቶስ መታመን አይፈልጉም ይሆናል። ለእንደዚህ ዐይነት ሰሚዎች፣ አንተ ማዘጋጀት የምትችለው በጣም ኃይለኛ መተግበሪያ ኃጢአታቸውን እንዲጠሉ እና ወደ ክርስቶስ እንዲሸሹ መምከር ነው። በስብከታችን ሁሉ፣ ወንጌልን በማሳወቅ በማበረታታትና በመምከር ተግባራዊ ለማድረግ መጣር አለብን።

እኛ ሰባኪዎች የእግዚአብሔርን ቃል በስብከታችን ላይ በሥራ ላይ በማዋል ረገድ ከሚያጋጥሙን አንዱ የተለመደ ፈታኝ ሁኔታ በአንድ የተለየ መልኩ ችግር ያጋጠማቸው ግለሰቦች ሰባኪው ለነሱ የሚሆን መተግበርያ አላዘጋጀልንም በሚሉበት ወቅት ነው። ትክክል ናቸው? የግድ ትክክል ላይሆን ይችላል። እያንዳንዱን የመተግበርያ ክፍል ደጋግመህ መናገር ስትጀምር የስብከቱ ውጤትህ ሊሻሻል ቢችልም እንኳ ኃጢአትን እንዲተዉ መምከርን መስበክ ስሕተት አይሆንም።

አንድ የመጨረሻ ማስታወሻ። ምሳሌ 23፥12 “ልባችሁን ወደ ተግሣጽ ጆሮቻችሁንም ለዕውቀት ቃል አድርጉ” ይላል። በእንግሊዘኛ ትርጉሞች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ተግባራዊ አድርጉ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ሁልጊዜ ማለት ይቻላል (ምናልባት ሁልጊዜ?) የሰባኪውን ሥራ (ሥነ ስብከት እንደሚያስተምረን) ወይም የመንፈስ ቅዱስን ሥራ (ስልታዊ ሥነ መለኮት  እንደሚያስተምረን) ሳይሆን ቃሉን በሚሰማ ሰው የሚተገበረውን ሥራ የሚያመለክት ይመስላል። እኛ የተጠራነው ቃሉን ለልባችን እንድንተገብር እና እራሳችንን ለዚህ ሥራ እንድናውል ነው።

ይህ ምናልባት በሚቀጥለው እሁድ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ጥቅም ልናደርገው የምንችለው ዋነኛው መተግበሪያ ነው።

ማርክ ዴቨር