መለወጥ (Conversion) ማለት ምን ማለት ነው?
መለወጥ የአቅጣጫ ለውጥ ማድረግ ማለት ነው። አንድ ሰው ከኅጢአት መንገድ ተመልሶ ለድነት ወደ ክርስቶስ ሲሄድ ማለት ነው። ይህም ከጣዖት አምልኮ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ፣ ራስን ከማጽደቅ ወደ ክርስቶስ ጽድቅ መሻገር ማለት ነው። ከራስ አገዛዝ ወደ እግዚአብሔር አገዛዝ መመለስ ማለት ነው።
መለወጥ የአቅጣጫ ለውጥ ማድረግ ማለት ነው። አንድ ሰው ከኅጢአት መንገድ ተመልሶ ለድነት ወደ ክርስቶስ ሲሄድ ማለት ነው። ይህም ከጣዖት አምልኮ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ፣ ራስን ከማጽደቅ ወደ ክርስቶስ ጽድቅ መሻገር ማለት ነው። ከራስ አገዛዝ ወደ እግዚአብሔር አገዛዝ መመለስ ማለት ነው።
ለብዙ ሰዎች የክርስቲያን የመለወጥ[1] አስተምህሮ ውብ ወይም ማራኪ አይደለም። አስገዳጅ ወይም ስሜት የሚረብሽ ነው ይላሉ፤ "ማንም ሰው እምነቱን በግድ አያሰርጽብኝም!” ወይም “እምነቴና አካሄዴ ስሕተት እንደሆነ የምትነግረኝ አንተ ማን ነህ!?” ይላሉ።
መለወጥ የቅዱሳት መጻሕፍት ዋና ሐተታ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን በርግጥ ለጠቅላላው የመቤዠት ታሪክ መሠረት ነው። በተለይም መቤዠት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ባለው ተዛምዶ ከመለወጥ ጋር ይያያዛል። ከመለወጥ ውጪ እግዚአብሔርን በማዳኑ መንገድ ማወቅ አንችልም። የኃጢአትን ይቅርታ ማግኘት አንችልም። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እና የማዳኑ መንግሥት መግባት አንችልም።
ሕብረት ፊተኛውን ቦታ መያዝ አለበት እየተባለ አይደለም። አንድ ሰው መጽደቅ "ስለ ነገረ ቤተ ክርስቲያን የመሆኑን ያክል ነገረ ድነት ተኮር አይደለም፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን የመሆኑን ያክል ድነት ተኮር አይደለም" በማለት የተናገሩትን የኤን. ቲ. ራይትን የታወቀ አባባል ሊያስብ ይችላል። "አዲስ ኪዳን ቅድሚያ የሰጠውን ኋላ ማድረግ፣ አዲስ ኪዳን ከኋላ ያሰፈረውን ደግሞ ፊት ማድረግ" የሚለው እውቅ የሆነ የዳግላስ ሙ አባባል ለዚህ ግልጽ ምሳሌ ይሆንልናል።
በብሉይ ኪዳን ላይ ተስፋ የተሰጠው ታሪክ፣ ማለትም በእባቡ ላይ የሚፈጸመው የእግዚአብሔር ድል ነሺነት ታሪክ (ዘፍጥረት 3፥15)፣ በአዲስ ኪዳን እውን ሆኗል። ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳንን፣ አዲስ ፍጥረትን፣ አዲስ ዘጸአትን፣ እና አዲስ ልብን ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቃል ገብቶ ነበረ። እናም አዲስ ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት፣ ሞት እና ትንሣኤ እነዚህ ተስፋዎች ሁሉ በድምቀት ፍጻሜ እንዳገኙ አውጇል።
በአሁኑ ጊዜ አብዛኛው ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ የምናየው አንድ ወጥ ታሪክ ነው ብሎ አበክሮ ይናገራል፤ እናም ትክክል ነው። ይህም ታሪክ አብዛኛውን ጊዜ ፍጥረት፣ ውድቀት፣ ቤዝዎት እና መጠቅለል በሚል ይተነተናል። ከፍጥረት ተነሥቶ አዲስ ፍጥረት ላይ የሚያርፍ ታሪክ ነው።